የአስተሳሰብ ሕግጋት ማለት ማናቸውም ስሜት የሚሰጡ ሐሳቦች ሊከተሉዋቸው የሚገቡ ሕግጋት ማለት ነው። ይህ ፈላስፎች በዘመናት ላይ ያገኙት አንድ የሥልጣኔ ምርት ነው። እነዚህ ሕግጋት እጅግ መሠረታዊ እና ሁሉም የዕውቀት ዘርፍ ሊከተሏቸው የሚገባ ብቻ ሳይሆን በዕለት ተዕለት ኑሮ ሳይቀር ሊተገበሩ የሚገቡ ናቸው። የሕግጋቱ ብዛት ሦስት ሲሆን እንደሚከተለው ይዘረዘራሉ፦
እዚህ ላይ ተቃራኒ ሲባል ዘመናዊና የጠራ ትርጉም አለው፣ አለበለዚያ እላይ የተጠቀሱት ህግጋት አይሰሩም። ለምሳሌ፦ ሁሉም ሰው ኬኒያዊ ነው ለሚለው ዓረፍተ ነገር ተቃራኒ ቢፈለግ፣ ሁሉም ሰው ኬኒያዊ አይደለም እሚል ይሆናል። ይሁንና ሁሉም ሰው ኬኒያዊ አይደለም ማለት ምን ማለት ነው? ማንም ሰው ኬኒያዊ አይደለም ማለት ነውን ወይንስ አንድ አንድ ሰዎች ኬኒያዊ አይደሉም ነው? የመጀመሪያው ዓይነት ተቃርኖ ተጻራሪነት ይባላል። ይሁንና በዘመናዊ ሥነ አመክንዮ ተቃራኒ ሲባል ሁለተኛው ዓይነት ተቃርኖን ወይም በሌላ አነጋገር መጣረስ እሚለውን ዓይነት መንገድ ይይዛል። በሌላ አባባል እዚህ ጽሑፍ ላይ ተቃራኒ ሲባል መጣረስን እንጅ ተጻራሪነትን አይወክልም።
ነጭ እና ጥቁር በተለምዶ ተቃራኒ ተደርገው ይወሰዳሉ። ስለሆነም በ ሕግ ፪ መሰረት፣ ሁሉም ነገር ወይም ነጭ ነው፣ ወይም ደግሞ ጥቁር ነው። ይሁንና ይሄ አስተሳሰብ ስህተት ነው። ሁሉም ነገር ነጭ ነው ሚለው አረፍተ ነገር ተቃራኒ ሁሉም ነገር ነጭ አይደለም እሚል ነው። ስለሆነም ሕግ ፪ እሚሰራው ለዚህ አረፍተ ነገር ነው።